በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ የአልመንድ ወተት
ሐና ኃይሌ
Homemade almond milk is healthy, delicious, and inexpensive than store-bought brands.
Prep Time 12 hours hrs
Making time 5 minutes mins
Total Time 12 hours hrs 5 minutes mins
Servings 4 ኩባያ
Calories 64 kcal
መፍጫ
የወንፊት ወይም የጨርቅ ማጥለያ
ትልቅ ጎድጓዳ ሳህን
የሚከደን የብርጭቆ ጠርሙስ ወይም ጆግ
- 1 ኩባያ ጥሬ የአልመንድ ለውዝ
- 2 ኩባያ የተጣራ ውሃ ለመዘፍዘፊያ
- 4 ኩባያ የተጣራ ውሃ ለመፍጫ
- 1 pinch ቁንጣሪ የባህር ጨው እንደ አስፈላጊነቱ
- 1/2 የሻይ ማንኪያ ቫኒላ እንደ አስፈላጊነቱ
- 2 የሾርባ ማንኪያ ማር ወይም ሌላ ማጣፈጫ እንደ አስፈላጊነቱ
ጥሬውን የአልመንድ ለውዝ ከተቻለ ሌሊቱን (ለ12 ሰዓታት) ወይም ቢያንስ ከ4-6 ሰአታት ክዳን ባለው ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ በውሃ መዘፍዘፍ፡፡ ለረጅም ሰዓት በውሃ ዉስጥ በተዘፈዘፈ መጠን ወተቱ የበለጠ ወፍራም ይሆናል፡፡
ከተዘፈዘፈ በኋላ ማጥለልና በንፁህ ውሃ ማለቅለቅ
በመፍጫ ውስጥ የተዘፈዘፈውን ለውዝ ፣ የተጣራ ውሃ ፣ ቫኒላ ፣ እና ማጣፋጭ መጨመር።
በከፍተኛ ሀይል ከ2-3 ደቂቃዎች መፍጨት፡፡
በወንፊት ወይም የጨርቅ ማጥለያ በመጠቀም በጎድጓዳ ሳህን ውስጥ ማጥለል፡፡ ከዚያም የተጣራውን የአልመንድ ወተት አየር ወደማያስገባ የብርጭቆ ጠርሙስ ማንቆርቆር፡፡
የአልመንድ ወተት እንዴት ማቆየት ይቻላል? አልመንድ ወተት ለ 3-4 ቀናት በማቀዝቀዣ ውስጥ ሊቀመጥ ይችላል፡፡ ወተቱ በማቀዝቀዣ ውስጥ ሲቀመጥ በተፈጥሮ ሊያጠል ይችላል፡፡ ከመጠቀምዎ በፊት በደንብ ይነቅንቁት፡፡
የጣዕም አማራጮች ጣዕም ለመጨመር እና ትንሽ ለማጣፈጥ 1/2 ኩባያ እንጆሪ በመጨመር የአልመንድ እንጆሪ ወተት ማዘጋጀት ይቻላል። የፈለጉትን ሌላም አይነት እንጆሪ መጠቀም ይቻላል፡፡ ለቸኮሌት ጣዕም ደግሞ 1-2 የሾርባ ማንኪያ የካካዋ ዱቄት መጨመርና አብሮ መፍጨት፡፡
የአልመንድ ገለባውን ምን ይደረግ? ወተቱን ከተሠራ በኋላ የአልመንድ ገለባውን አለማባከን፡፡ አንደኛ እንደ አልመንድ ዱቄት ሆኖ ሊያገለግል ይችላል፡፡ መጀመሪያ ገለባውን በኩኪስ ወረቀት ላይ ማድረግ እና በዝቅተኛ ሙቀት ባለው ምድጃ ውስጥ ማድረቅ፡፡ ከዚያ ፣ በምግብ ወይም በጭማቂ መፍጫ መፍጨት፡፡ ወይም በምድጃው ውስጥ ከደረቀ በኋላ በቤት ውስጥ ለሚዘጋጅ ግራኖላ (granola) መጠቀም፡፡ ወይም በቀጥታ በማቀዝቀዣ ውስጥ በማስቀመጥ ከፍራፍሬዎች ጋር አብሮ በመጭመቅ መጠቀም ይቻላል፡፡