Join us for a captivating conversation with Melat Mamo, (MPH, licensed ASCP), and mother of two, as she shares her journey of healing her son from eczema through the GAPS diet.
Discover insights into nutrition, motherhood, and life in Abu Dhabi as Melat offers valuable advice and personal experiences. Tune in for an inspiring discussion on holistic wellness and the power of nutrition in transforming lives.
ስለ GAPS አመጋገብ ፣ እናትነት እና ኑሮ በአቡዳቢ ከሜላት ማሞ (MPH, licensed ASCP)
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከሜላት ማሞ ጋር ስለ እናትነት ፣ በቤት ውስጥ ሙሉ ጊዜ መሆንና ቤተሰብን መንከባከብ ፣ እና ስለ ኑሮ በአቡዳቢ ተጨዋውተናል።
በሰፊው የልጇን የቆዳ ህመም (Eczema) ለማዳን እና ለቤተሰቧ ጤና የረዳትን የ GAPS (Gut and Psychology Syndrome) የአመጋገብ ልምድ ላይ ያላትን እውቀትና ልምድ እንዲሁም የለት ተለት ተሞክሮ አካፍላናለች።ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት እርግጠኛ ነኝ። መልካም ቆይታ!!
ሜላት የሁለት ልጆች እናት ናት። በሙያዋ የማህበረሰብ ጤና ስፔሻሊስት እና licensed ASCP ናት። በአሁን ጊዜ ሙሉ ጊዜዋን በቤት ውስጥ በመሆን ልጆችዋን በማሳደግ እና ቤተሰብዋን በመንከባከብ ላይ ትገኛለች።
ማሳሰቢያ:- ይህ መረጃ የግል ልምድ እንደማስተማሪያ እንዲሆን የቀረበ ነው። የህክምና ምክር አይደለም። ለግል ጤና የህክምና ባለሙያ ያማክሩ!!
Leave a Reply