ዳውን ሲንድረም
በእናትHood የተለያዩ የማህበረሰብ ሚዲያ አማካኝነት ከዚህ ቀደም ስለ ልዩ እንክብካቤ የሚያሻቸው ህፃናት (special needs kids) አንስተን በምንወያይበት ጊዜ ያስተዋልነው አንድ ነገር ቢኖር ዳውን ሲንድረም ስለተሰኘው የጤና እክል እኛ የ ሀበሻው ማህበረሰብ ያለን መረዳት እና ግንዛቤ እስከዚህም መሆኑን ነበር። ሌላው ቀርቶ የቃሉን ተገቢ አቻ ፍቺ በቋንቋችን አለመኖሩ ስለ ነገሩ ያለን እውቀት ውሱን ስለመሆኑ አንዱ ምስክር ነው። ከዚህም የተነሳ ከዳውን ሲንድረም ጋር የሚኖሩትን ወገኖቻችንን በመልካም አይን ለማየት ስንቸገር እንስተዋላለን። የወላጆቻቸው ኩነኔ መቀጣጫ ማሳያ ናቸው የሚል ፈፅሞ የተሳሳተ አመላካከት ፤ ቡዙውን ጊዜ ልጆቹ በቤት ውስጥ ከማህበረሰቡ ተሸሽገው እንዲኖሩ አስገድዷቸዋል።