Join us as we explore the remarkable journey of an Ethiopian mom living in Rwanda who traveled to the US to seek midwife care and experience an out-of-hospital birth. Discover her motivations, the challenges she faced, and the cultural insights she gained along the way.
Hiwote Tadesse is a mom of three with a background in Public Health (MPH). Throughout previous podcast episodes, she has engaged in numerous conversations about nontoxic living and breastfeeding.
This episode is part two of a continued discussion. In first part of the episode she shared her personal journey, including her mixed-racial marriage to a Kenyan husband, her experiences in motherhood, and more.
She also runs a YouTube channel where she shares insights on homesteading, nontoxic living, motherhood, and other lifestyle topics.
ከሆስፒታል ዉጪ ለመውለድ ከሩዋንዳ ወደ አሜሪካ ፤ ለምን? ከህይወቴ ታደሰ ጋር (MPH)
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ ታደሰ ጋር ስለ ሶስተኛ ልጇ የወሊድ ዝግጅት ፣ ለምን ከሩዋንዳ ወደ አሜሪካ ተጉዛ ከሚድዋይፍ ጋር ለመውለድ እንዳቀደች ፣ የእናትነት ጉዞዋን እና ለሎችም ተያያዥ ነገሮችን ተጨዋውተናል። በጣም ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች።
ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። ጥያቄ ካላችሁም ብትልኩልን እንመልሳለን።
ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ ወይም ለወዳጅ ለቤተሰብ አካፍሉት።
ህይወቴ የሶስት ልጆች እናት ናት። እንደ እቅድዋና ምኞትዋ ሶስተኛ ልጇን በማዋለጃ ማዕከል (Birthing Center) ፍፁም ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ወልዳለች። እንኳን ደስ አለሽ እያልን በተከታታይ ስላካፈለችው ልምድ እናመሰግናታለን።
ህይወቴ በማህበረሰብ ጤና ማስተርስ አላት (Masters of Public Health) ጤናማ ተፈጥሮአዊ አኗኗር ላይ ትኩረት ታደርጋለች። ህይወቴ ጤናን ከተለመደው የህክምና እና በመድሀኒት ማከም በተለየ መልኩ አማራጭና ሁሉን አቀፍ የሆነ ወይም alternative and holistic health የተሟላ ጤና ፣ ከመርዛማ ንጥረ ነገሮች (toxins exposures) የነፃ አካባቢን በመፍጠር በሽታን እንዴት መቀነስና ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙን እንዲያጎለብት የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በIG & YT ታካፍላለች።
በቤት በመሆን ሙሉ ጊዜዋን ሶስት ልጆችዋን እያሳደገች በሩዋንዳ ኪጋሊ ትኖራለች። በጊቢዋ የጓሮ አትክልቶች ትተክላለች ፣ ዶሮዎችን ታረባከች። እንዲሁም ከቤተሰቧ ጋር ጉዞ ማድረግ ታዘወትራለች። ልጆቿን ከአንድ በላይ ቋንቋ ለማስተማር የምትጥር ዘመነኛ ኑሮን ከባህል ጋር ያጣመረች እናት ናት።
Leave a Reply