In this podcast episode, join us for an enlightening conversation with a mom of three and MPH expert as she shares her journey of preparing for her third baby.
We discuss her pregnancy, life in Rwanda’s bustling city of Kigali, and the dynamics of her mixed-race marriage with her Kenyan husband.
Discover how she balances family life, cultural differences, and holistic wellness. Get inspired by her unique experiences and insights into living a fulfilling and non-toxic lifestyle.
Hiwote Tadesse is a mom of three with a background in Public Health (MPH). Throughout previous podcast episodes, she has engaged in numerous conversations about nontoxic living and breastfeeding.
She also runs a YouTube channel where she shares insights on homesteading, nontoxic living, motherhood, and other lifestyle topics.
ወሊድ በአሜሪካ ከሆስፒታል ውጪ ፣ እናትነት ፣ ኑሮ በሩዋንዳ እና ጉዞ ከህይወቴ ታደሰ ጋር
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ ታደሰ ጋር ስለ ሶስተኛ እርግዝናዋ እንዴት ለወሊድ እየተዘጋጀች እንዳለች ፣ እናትነት ፣ በተለያዩ አገራትና ባህል ልጆችን ማሳደግ ፣ ወሊድ በሆስፒታል እና በማዋለጃ ማዕከል (birthing center) እና የመሳሰሉትን ነገሮች ተጨዋውተናል።
መልካም ቆይታ።
ህይወቴ የሶስት ልጆች እናት ናት። በማህበረሰብ ጤና ማስተርስ አላት (Masters of Public Health) ጤናማ ተፈጥሮአዊ አኗኗር ላይ ትኩረት ታደርጋለች። ህይወቴ ጤናን ከተለመደው የህክምና እና በመድሀኒት ማከም በተለየ መልኩ አማራጭና ሁሉን አቀፍ የሆነ ወይም alternative and holistic health የተሟላ ጤና ፣ ከመርዛማ ንጥረ ነገሮች (toxins exposures) የነፃ አካባቢን በመፍጠር በሽታን እንዴት መቀነስና ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙን እንዲያጎለብት የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በIG & YT ታካፍላለች።
ህይወቴ በቤት በመሆን ሙሉ ጊዜዋን ልጆችዋን እያሳደገች በሩዋንዳ ኪጋሊ ትኖራለች። በጊቢዋ የጓሮ አትክልቶች ትተክላለች ፣ ዶሮዎችን ታረባከች። እንዲሁም ከቤተሰቧ ጋር ጉዞ ማድረግ ታዘወትራለች። ልጆቿን ከአንድ በላይ ቋንቋ ለማስተማር የምትጥር ዘመነኛ ኑሮን ከባህል ጋር ያጣመረች እናት ናት።
Leave a Reply