EnatHood podcast is dedicated to motherhood and what a mothers cares for. It covers a range of topics, including pregnancy, childbirth, baby care, parenting, and healthy lifestyle choices. It is brought to you by Hana Haile.
እንኳን ደህና መጣችሁ! Welcome!
የእናትHood | EnatHood ፖድካስት ስለ እናትነትና እና እናት ስለሚመለከታት ሁሉ ነገር ላይ ትኩረት የሰጠ ፖድካስት ነው። እርግዝና ፣ ወሊድ ፣ የልጅ እንክብካቤ ፣ ወላጅነት እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ምርጫዎችን ጨምሮ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን ይሸፍናል።
Subscribe to the show via
አዘጋችቼ የማቀርብላችሁ እኔ ሐና ኃይሌ ነኝ። የሶስት ልጆች እናት ነኝ። የሙሉ ጊዜ ስራዬ ቤተሰቤን መንከባከብ ነው። የቤት እመቤት ነኝ። የምኖረው ቴክሳስ ነው። የእናትነት ጉዞዬን ልምድ ፣ ለተፈጥሮአዊ የአኗኗር ዘዴ ያለኝን ጥልቅ ስሜት እና እናትን እና ልጆችን የተመለከቱ ወቅታዊ ጉዮች ላይ ውይይት ማድረግ ያስደስተኛል። የእናቶች የወሊድ ታሪክ መስማትና ማንበብ እወዳለሁ።
የእናትHood መድረክ በእናትነት ጉዞ ውስጥ የተማርነውን ልምዶች የምንለዋወጥበት ፣ ስለ ወላጅነት ጠቃሚ ምክሮችን እና ዘዴዎችን የምንማማርበት እንዲሁም በአለም ዙሪያ ካሉ እናቶች ጋር የምንገናኝበት ቦታ ማለትነው።
ስለ እርግዝና እና ወሊድ፣ እንዲሁም ስለ ልጆቻችንን አካላዊ እና አይምሮአዊ ጤና ፣ እና በአጠቃላይ የቤተሰባችንን ጤንነት የተመለከቱ ጉዳዮችን በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች ጋብዘን ዘመኑ የደረሰበትን መረጃ እና ሳይንሳዊ ግኝቶችን እናካፋላለን።
በጠቅላላው እናትን የተመለከተ የማንነካው ርዕስ አይኖርም። ማህበረሰባችን ፊለፊት የማያወራቸው ወይም አወዛጋቢ እና አከራካሪ የሚባሉ ርዕሶችን ሳይቀር መረጃን አስደግፈን እና የግል ምርጫን አክብረን ስርአቱን የጠበቀ ውይይት እናካሂዳለን። በተጨማሪም የአገራችን ባህልና ልምድ እየፈተሽን በጎውን ለልጆቻችን እናወርሳለን።
እንዲሁም በቁጥር ብዙ ከሆኑ እናቶች ጋር ውይይት ይኖረናል። ከህይወት ጉዞ ልምዳቸውና ታሪካቸው ዕውቀት እንቀስማለን። የወሊድ ታሪኮችን እንሰማለን። ደስታናም ሆነ ሀዘናችንን በጋራ እየተካፈላለን እንቀጥላለን።
ስለዚህ የእናትHood ቤተሰብ እንድቀላቀሉ እየጋበዝኩኝ፤ ኑ! የእናትነት አስደሳችና ፈታኝ ጉዞ በአንድ ላይ እንጓዝ እላለሁ።
ዉይይቶቻችን መረጃ ሰጪ፣ ጠቃሚ እና አነቃቂ እንደሚሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ። የበለጠ መረጃ ከ enathood.com ማግኘት ትችላላችሁ። እንዲሁም መልዕክት ካላችሁ በእናትhood ድህረገጽ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች አድርሱኝ። አብራችሁኝ ስለቆያችሁ አመሰግናለሁ። በቀጣይ ተከታታይ ክፍሎች እንገናኝ።
በያላችሁበት ቸር ይግጠማችሁ። ሠላም!!
Leave a Reply