“የእናቶች ቀን” አጋጣሚን በመጠቀም ለሁሉም እናቶች ደብዳቤ ለመፃፍ ፈለኩኝ፡፡
በአጠቃላይ እናቶችን ለማክበር የእናቶች ቀን ሀሳብን አልቃወምም። ነገር ግን ዛሬ የደረስንበት የአንድ ቀን ብቻ ፣ ከመጠን በላይ በንግድ የታጀበ የእናቶች ቀን አካል የመሆን ፍላጎት የለኝም ፣ አድናቂም አይደለሁም፡፡
በብሔራዊ የችርቻሮ ፌዴሬሽን (National Retail Federation) መረጃ መሠረት እ.ኤ.አ. በ 2021 በአሜሪካ ብቻ ለእናቶች ቀን ስጦታ ወደ 2.8 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገደማ ይወጣል ተብሎ ታቅዷል፡፡
የገበያ ባለሙያተኞች ለእናቶች ቀን የሸማቾችን ስሜት ለመቆጣጠር በጣም ይጥራሉ፡፡ ለእናቶች ቀን ስጦታ መግዛት ስሜታዊ የግብይት ተሞክሮ ሊኖረው ይችላል።
እናም አስተዋዋቂዎች እነዚያን ስሜቶች በግብይት ዘመቻዎቻቸው እንደ መሳሪያ ይጠቀማሉ፡፡ ለማስታወቂያዎች ትንሽ ተጨማሪ ትኩረት ከሰጣችሁ እና ካጤናችሁ ምን ያህል የሚገፋፋ እንደሆነ እና የእናቶች ቀን እንዴት ትልቅ ንግድ እየሆነ እንደመጣ በፍጥነት ትገነዘባላችሁ፡፡
በእናቶች ቀን ለውጥ እናመጣ
ሰዎች ብዙውን ጊዜ እንዲህ በማለት ይጠይቁኛል “ከልጅሽ ጋር ቤት ተቀመጠሻል ፣ ወይንስ ስራ ትሰሪያለሽ?”
ይህ ጥያቄ ይረብሸኛል። ምክንያቱም የጥያቄው ቃና ብዙውን ጊዜ የእናትነትን ሚና ያሳንስብኛል፡፡
በመጀመሪያ እናት መሆን የሙሉ ሰዓት ሥራ ነው!! ሲቀጥል የግል ምርጫ ነው። ሦስተኛ በቤት ውስጥ ከልጅ ጋር መሆን ቁጭ ብሎ መዋል ማለት አይደለም፡፡ ሁሉም እናቶች በውጭ ሥራ ኖራቸውም አልራቸውም ጠንክረው እንደሚሠሩ አምናለሁ፡፡
በዓለም ላይ በጣም ከባድ ሥራ እናትነት ነው፡፡
ደግሞም እናትነት የሚመጣው ከከፍተኛ ኃይል እና ሃላፊነት ጋር ነው። ተተኪውን ትውልድ እያሳደግን ነው፡፡ የሰውን አእምሮ እና ልብ እየቀረፅን ነው፡፡
ስለሆነም የእኔ በትህትና የተሞላ ሀሳብ ይህን ይመስላል።
Let’s use this one day that is given to mothers to magnify our everyday’s motherhood role:
- በዚህ ዓመት ትንሽ ጊዜ ወስደን በዙሪያችን ግንዛቤን እንፍጠር፡፡ የእናትነት ስራችን ከማንኛውም በላይ አስፈላጊ እና ሊከበር የሚገባው ነው።
No mom to be shamed just because she is a mother. She is raising a human being!!
- ጥንካሬያችንን በባለቤትነት እንያዝ ፣ በውስጣችን ያለውን የእናትነት ተፈጥሮአዊ አስተዋይነት (mother instincts) በጭራሽ አንጠራጠር እና እናትነትን ሙሉ በሙሉ እንቀበል፡፡
Mother’s intuition (gut feeling), I call it mom wisdom, is real and can help us make decisions.
I am sure many of you have experienced it. Don’t you remember an incident where you just know something is wrong with your child playing outside and you found out it is true, or you just know something in your gut and fail to explain it analytically?
There is a science behind it, and God (the creator, whatever you call it) has a reason giving us this amazing connection and wisdom.
ስለዚህ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን አስፈላጊ ውሳኔዎችን ለማድረግ ጥበባችንን እንጠቀምበት፡፡ በቀላሉ በቃላት ለመግለፅ ስላልቻልን ብቻ ኃይላችንን አሳልፈን አንስጥ፡፡
I have seen teachers or doctors, or any other professional in institutions who interact with our children try to make decisions by themselves for our children by disregarding their mother’s opinion.
We should stand by our opinion, our intuition, or our wisdom and be able to say I am the mother of this child and my opinion should be heard, or I need more time, or you should just speak your gut feelings.
- የጋራ ኃይላችንን ለተሻለ ነገር እንጠቀምበት፡፡
በዓለም ላይ የወጪ ውሳኔ እኛ እናቶች እንደምንቆጣጠር የማይካድ እውነታ ነው። ለዚህም የቤት አስቤዛ ወጪን መመልከት በቂ ነው። ስለዚህ እኛም ሆነ የመጪው ትውልድ ጤና የተሟላ እንዲሆን በገንዘባችን የተሻለ ውሳኔ በማድረግ የምግብ ኢንዱስትሪው ጤናማ ምግብ እንዲያመርት የበኩላችን አስተዋፆ እናድርግ፡፡
Happy Mother’s Day, Every Single Day!!
I don’t think “Mother’s Day” is any more special than the day I found out I am pregnant and become a mother. How does this one day a better day to celebrate more than the nine-plus months of carrying a baby inside?
How is this one day greater than three days I spent laboring to give birth? How come this one day is a better day than many many sleepless nights I took care of a baby?
So, I believe mothers should be honored not only ONE day of the year but the whole year, 365 days!!
እኛ እናቶች በዓመት ውስጥ እያንዳንዱን ቀን ፣ ሰዓት ፣ እና ደቂቃ ስራ ላይ ነን፡፡
እነሆ… ለሁሉም እናቶች !! ...
ከልጆቻቸው ጋር ሙሉ ሰዓት በቤት ለሚቆዩ እናቶች
ሰራተኛ የሆኑና በውጭ ሚና ያላቸው፣ እንዲሁም ልጆቻቸውንም የሚንከባከቡ እናቶች ፣
ለእንጀራ እናቶች ፣
ለአያቶች እና ለቅድመ አያቶች ፣
ልጆቻቸውን በህይወት ላጡ እናቶች ፣
mothers who are expecting and wish to become a mother.
I wish you all Happy Mother’s Day today, and every single day!!
Your hard work and sacrifices have values; the world sees the fruit of your work.
Who is a stay-at-home-mom like me? Would you do your part to make the needed changes? What other changes can we bring together? Let me know in the comment below.
Amit Chomal
It very helpful thank you for this informations.
ሐና ኃይሌ
Thank You!!
Yamrot
እይታሽን ሳያደንቁ እና በርቺ ሳይሉ ማለፍ ከባድ ሆነብኝ።
በትክክል ገልጸሽዋል እናትነት በ አንድ ቀን አድናቆት ብቻ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም።
በርቺ !
ሐና ኃይሌ
አመሰግናለሁ ያምሮቴ!!
እንዳልሽው ነው እናትነት በ አንድ ቀን አድናቆት ብቻ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም።
Fenteseya
“Happy mother’s day, today and everyday” to you too!
ሐና ኃይሌ
Thank you Enuye!!
Meseret
ግሩም የሆነ በሳል መልዕክት ስላጋራሽን ከልብ አመሰግናለሁ ፣
እኔም እዚህ ላይ የሚሰማኝን ሀሳብ ለመጨመር የውጭ ባህሎችን አለመቃወም፣በተለይ ጥሩዎችን እንዳለ ሆኖ እኔ የማምነው ግን የራሳችን የሆነውን አገር በቀል ባህል እና ወጎቻችንን አጥብቀን ብንይዝ፣ ሁሌም የተሰጠንን ተቀባይ ብቻ ባንሆን ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም ያላያናቸው፣ያልሰራንባቸው እጅግ ውብ እና ጠቃሚ ደግሞም የግላችን ወግ እና ባህልየሆኑ ብዙ ነገሮች ስላሉን ማለት ነው።ስለዚህ ቫላንታይን፣ቤቢ/ዊድንግ ሻወር….. ትተን የራሳችንን ለልጆቻችን ብናስተምር ብዙ ጥቅም አለው ብዬ አስባለሁ፣ በርች፣በጣም ጥሩ ሀሳብ ነው።
ሐና ኃይሌ
ሰላም መሰረት
ስለ ገንቢ አስተያየቶሽ በጣም አመሰግናለሁ!!
ከሀሳብሽ ጋር በጣም እስማማለሁ። ወደፊት ባነሳሻቸው ሀሳቦች ላይ ፅሁፎችን አዘጋጃለሁ። ደጋግመሽ ወደ እናትHood በመምጣት ተከታተይ።
Kidsna
Thank you Hani for the powerful message! መልካም የናቶች ቀን to you and to all beautiful and strong Mother’s including me and to the single Father’s who raised there children as a mother and father as well! 🍾💐
Tigist
Hanniye thank you for sharing this wonderful message. Stay blessed 🙏🏾