ልጆች ተኮር አመጋገብ (Baby – Led Weaning) ከጊፍቲ ባዮ ጋር የተደረገ ቆይታ
በዛሬው የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከጊፍቲ ባዮ ጋር ቆይታ ይኖረናል። ዉይይታችን ልጆች ተኮር አመጋገብ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። ህፃናት ልጆች በተለይም ከስድስት ወር በኃላ ተጨማሪ ምግብ እንዴት እናስጀምራለን? ምን አይነት የአመጋገብ ዘዴዎች አሉ? ፣ እንዲሁም እንዴት ተመጣጣኝ ምግብ መመገብ እንችላለን? እና ህፃናት እራሳቸውን መመገብ እንዲችሉ እንዴት መርዳት እንምንችል ጨምሮ ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮችን እናነሳለን አብራችሁን ቆዮ።
ጊፍቲ የሁለት ወንድ ልጆች እናት ስትሆን በሙያዋ ደግሞ የግራፊክስ ዲዛይነር ነች። በአሁን ጊዜ ላይ ሙሉ ጊዜዋን በቤት ውስጥ በመሆን ልጆችዋን በማሳደግ ላይ ትገኛለች። ጊፍቲ ኑሮዋን ያደረገችው በአሜሪካ ዲሲ-ሜሪላንድ-ቨርጂኒያ ግዛት ውስጥ ሲሆን ተፈጥሮአዊ እና ጤናማ ኑሮ ትከተላለች። በኢንስታግራም/Instagram/ የማህበራዊ ሚዲያ የምታጋራውን ከተመለከታችሁ በቤት ውስጥ የምታዘጋጃቸውን ምግቦች ፣ ለልጆችዋ የምትከተለውን የአመጋገብ ዘዴና ሌሎች ብዙ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ልምዶችን ታገኛላችሁ።
Leave a Reply