የቤት ዉስጥ ት/ት፣ የሁለት ቋንቋ ተናጋሪነት እና ከስክሪን ነጻ የሆኑ ልጆች ከቤተልሔም ፀጋዬ ጋር የተደረገ ውይይት
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከቤተልሔም ፀጋዬ ጋር በቤት ውስጥ ልጆችን በሙሉ ሰዓት ማስተማር ፣ የሁለት ቋንቋ ተናጋሪ መሆን እና ልጆችን ከስክሪን (ከቲቪ እና ከስልክ) ነፃ አድርጎ ስለማሳደግ ተነጋግረናል። ቤተልሔም ብዙ ጠቃሚና አነቃቂ መረጃዎችን ከወላጅነት ልምዷ ጨምራ አካፍላናለች። መልካም ቆይታ።
ቤተልሔም የሁለት ልጆች እናት ስትሆን ልጆችዋን በሙሉ ጊዜ በቤትዋ ት/ቤት ሳትልክ ታስተምራለች። ልጆችዋ አማርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋ አቀላጥፈው ይናገራሉ። ከዛም ጋር በተገናኘ የአማርኛ ቋንቋ ማስተማርያ የርቀት (በዙም) የምታስተምርበት ፋኖስ የሚባል ማስተማርያ አላት። በተጨማሪም ቤተልሔም የልጆች መማርያ መፅሀፍትንም ታዘጋጃለች። ከፋኖስ ድህረ ገፅ እነዚህን የአማርኛ መማርያ መፅሀፋትና ሌሎች መርጃ መሳሪያዎች ታገኛላችሁ። ሙሉ መረጃ ለማግኘት ይህን ሊንክ ይጠቀሙ።
Leave a Reply