ምጥን ያለ ፍርሃት
ሁሌም እንደምለው እና ዛሬም በ አንክሮ የምደግመው ነገር ቢኖር ሁላችንም ወላድ እናቶች የወሊድ ታሪኮቻችንን ወደ ፊት በማምጣት ልንነጋገርባቸው ፣ ልንማማርባቸው እንዲሁም በቃል ያለ ይረሳል በፅሁፍ ያለ ይወረሳል እንዲሉ ወረቀትን ከብዕር አገናኝተን ልንሰንዳቸው ይገባል። ለዚህም ሲባል ዛሬ የእናት ጊፍቲን ተፈጥሮአዊ የወሊድ ታሪክ ይዤላችሁ ስቀርብ በታላቅ ሀሴት እና ክብር ነው። ጊፋቲንም ታሪክሽን ስላጋራሽን ምስጋናችን የላቀ ነው እንላለን፤ ይልመድብሽ። አንባቢዎች መቼም የወሊድ ታሪኳን አሁን የምናነብላት ጊፋቲ ለመሆኑ ማን ነች ብላችሁ ሳትጠይቁ አትቀሩም። ላስተዋውቃችሁ።







