የእናት ጡት ወተት ጥቅም ለልጆች
August Breastfeeding Awarness Month
የነሀሴን ወር የጡት ማጥባት ግንዛቤ ወር መሆኑን አስመልክተን በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ በቀለ ጋር ስለ የእናት ጡት ወተት ለልጆች ያለውን ጥቅም ተወያይተናል። እናም ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች።
በተጨማሪም በህይወቴ የYouTube channel ላይ ጡት ማጥባት ለእናቶች ያለውን ጥቅም ተወያይተናል። በጣም ጥሩ መረጃዎችን የያዘ ነው። እንደትመለከቱት እጋብዛችሁአለሁ።
ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። እንዲሁም ጥያቄ ካላችሁም ብትልኩልን እንመልሳለን።
💫ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ ወይም ለወዳጅ ለቤተሰብ አካፍሉት።
ህይወቴ የሁለት ልጆች እናት ናት። በማህበረሰብ ጤና ማስተርስ አላት (Masters of Public Health) ጤናማ ተፈጥሮአዊ አኗኗር ላይ ትኩረት ታደርጋለች። ህይወቴ ጤናን ከተለመደው የህክምና እና በመድሀኒት ማከም በተለየ መልኩ አማራጭና ሁሉን አቀፍ የሆነ ወይም alternative and holistic health የተሟላ ጤና ፣ ከመርዛማ ንጥረ ነገሮች (toxins exposures) የነፃ አካባቢን በመፍጠር በሽታን እንዴት መቀነስና ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙን እንዲያጎለብት የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በInstagram & Youtube ታካፍላለች።
ህይወቴ በቤት በመሆን ሙሉ ጊዜዋን ሁለት ልጆችዋን እያሳደገች በሩዋንዳ ኪጋሊ ትኖራለች። በጊቢዋ የጓሮ አትክልቶች ትተክላለች ፣ ዶሮዎችን ታረባከች። እንዲሁም ከቤተሰቧ ጋር ጉዞ ማድረግ ታዘወትራለች። ልጆቿን ከአንድ በላይ ቋንቋ ለማስተማር የምትጥር ዘመነኛ ኑሮን ከባህል ጋር ያጣመረች እናት ናት።
[…] ወር የጡት ማጥባት ግንዛቤ ወር መሆኑን አስመልክተን በተከታታይ የጡት ማጥባት ዉይይቶችን […]